Mission

Our Mission (ተልዕኮአችን)

ተልዕኮአችን/አላማችን:

ተልዕኮ (አላማ) “ወደ ራዕያችን ለመድረስ ምን ማድረግ አለብን” የሚለውን ጥያቄ ይመልሳል። እግዚአብሄር ወደ ራዕያችን እንድንደርስ ምን እንድናደርግ ይፈልጋል። በኢትዮጵያ ወንጌላዊት ቤተክርስቲያን እግዚአብሄር ወደ ሰጠን ራዕይ ለመድረስ የሚከተሉትን 5 አላማዎች ለመፈጸም እንተጋለን።

1) እውነተኛ አምልኮ

  • • አምልኮ በአጠቃላይ በዕለት ከዕለት ኑሮአችን የፈጠረንን እግዚአብሄር አምላካችንን ደስ ማሰኘት ነው።
  • • አምልኮ ማናቸውንም ለእግዚአብሄር የምንሰጣቸውን አገልግሎቶች በላቀና ትጋት በሞላበት መንገድ እየተወጣን እግዚአብሄርን ደስ ማሰኘት ነው።
  • • አምልኮ ፤ የቤተክርስቲያናችንን አላማ ወደ ፍጻሜ ለማድረስ እይታ ባለው እምነት ለመነሳት ፈቃደኞች በመሆንና ፤ በእግዚአብሄር ላይ በመታመን የእምነት እርምጃዎችን በመውሰድ ፤ እግዚአብሄርን ደስ ማሰኘት ነው።

2) እውነተኛ ህብረት

  • • እውነተኛ ህብረት የክርስቶስ አካል አንዱ ብልት ወይም አባል መሆን ነው።
  • • እውነተኛ ህብረት ፤ ሰዎችን አክብሮት በተሞላበት ፤ እንዲሁም ፍጹም ትህትናና ገርነት ባለበት ፍቅር በማስተናገድ የክርስቶስ አካል አባል ማድረግ ነው።

3) እውነተኛ ደቀመዝሙርነት

  • • እውነተኛ ደቀመዝሙርነት በዕለት ከዕለት ኑሮአችን የእግዚአብሄርን ልጅ ጌታ ኢየሱስ ክርስቶስን መምስል ነው።
  • • እውነተኛ ደቀመዝሙርነት ፤ የሰዎችን ህይወት የመቀየርና የመለወጥ ሃይል ባለው የወንጌል መልዕክት ሰዎች ክርስቶስን እንዲመስሉ ማድረግ ነው።
  • • እውነተኛ ደቀመዝሙርነት ፤ ሰዎች ሙሉ በሙሉ የተሰጡ የክርስቶስ ተከታዮች እንዲሆኑ የአገልግሎታችን አላማ በማድረግ ሰዎች ክርስቶስን እንዲመስሉ ማድረግ ነው።

4) እውነተኛ አገልግሎት

  • • እውነተኛ አገልግሎት ፤ የእግዚአብሄርን ፍቅር ፤ ሌሎችን በማገልገል መግለጥ ነው።
  • • እውነተኛ አገልግሎት ፤ ማንኛውም አማኝ ከእግዚአብሄር የተሰጠው ወይም እግዚአብሄር በእርሱ ውስጥ ያስቀመጠው የአገልግሎት ፀጋ እንዳለው አውቆ በዛ በተሰጠው ፀጋ እግዚአብሄርን በሙሉ ልቡ ማገልገል ነው።
  • • እውነተኛ አገልግሎት የሚገለገለው ሃይማኖታዊ በሆነ መንገድ ሳይሆን ለሚደረሰው ስው ትርጉም ባለውና የሚደረሰው ሰው ሊረዳው ወይም ሊገነዘበው በሚችልበት ደረጃ መሆን አለበት። ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ እንዲሁም ሐዋሪያው ጳውሎስ እራሳቸውን ዝቅ በማድረግና የሚደርሱዋቸውን ሰዎች በመምሰል የአገልግሎትን ምሳሌነት ትተውልን አልፈዋል።

5) እውነተኛ የወንጌል ስርጭት

  • • እውነተኛ የወንጌል ስርጭት ፤ የእግዚአብሄርን የማዳን የምስራች ቃል ላልደረሳቸው ማድረስ ነው
  • • እውነተኛ የወንጌል ስርጭት ፤ እግዚአብሄር በአምሳሉ ስለፈጠራቸው ሰዎች ግድ እንደሚለው ሁሉ እኛም ስለ እነዚህ በእግዚአብሄር አምሳል ስለተፈጥሩ ሰዎች ግድ ብሎን የእግዚአብሄርን የማዳን የምስራች ቃል ላልደረሳቸው ለማዳረስ መትጋት ነው።
  • • እውነተኛ የወንጌል ስርጭት ፤ ቤተክርስቲያናችን ፤ በሚገኝበት ማህበረሰብ ውስጥ ፤ ወንጌል ሊያመጣቸው የሚገቡትን ውጤቶች እንዲከሰቱ መሳሪያና ምክኒያት እየሆኑ የእግዚአብሄርን የማዳን የምስራች ቃል ላልደረሳቸው ለማዳረስ መትጋት ነው።

Our Purpose (Mission):

Our Purpose (Mission) statement defines our areas of focus to that will allow us to reach our vision. Our
purposes here in Ethiopian Evangelical Church in Baltimore are:

1) Genuine Worship

  • •Pleasing God in everything that we do
  • •Doing everything that we do for God with excellence
  • •Having visionary faith to accomplish our mission and take risk for God, depending on Him for
    everything

2) Genuine Fellowship

  • •Making people an active member of the body of Christ
  • •Building a church family where all people will treat be treated with dignity, respect and
    courtesy
  • •Building a church family that reflect the love and unity of God

3) Genuine Discipleship

  • •Teaching people to come to the maturity of Christ likeness in their day to day life
  • •Transforming people’s life into the image of Christ by the message of God’s word, which is
    the only agent that has the power to do so.
  • •Making the epic focus of our ministry the transformation of people into fully devoted
    followers of Jesus Christ

4) Genuine Ministry

  • •Expressing God’s love by serving others
  • •Recognizing that every believer has a God-given spiritual gift and thus has an area of
    ministry and helping the believers to discover, nurture and use their gifts to make a
    difference in the Kingdom of God.
  • •Understanding that ministry and evangelism must be carried out in a relevant way, making
    Jesus Christ relevant in the daily life of each person being reached, not in a vague and
    religious manner.

5) Genuine Evangelism

  • •Proclaiming the saving good news of Christ to those that have not committed to Christ yet.
  • •Caring for people, whom God has created in His own image, as He cares for them, and
    diligently laboring to reach them with the saving message of the gospel.
  • •Understanding that evangelism should have a visible impact around the community in which
    the church exits and laboring with dedication to bring about this kind of impact within the
    community.